Skip to content
HeyJared

The Rising South

የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

Podcast · By ወሰንሰገድ አሰፋ · English · Official site

Indexed episodes, last 90 days
22
Latest publication
Sep 3, 2026
Audience
Checking…
Earliest in this view
Jul 9, 2026

Latest episodes

  1. Episode · Sep 3, 2026

    የአፍሪካ ቀንድ በባለብዙ-ዋልታ ዓለም፦ የጂኦፖለቲካ የስበት ማዕከልነትና ሉዓላዊ ውሳኔ (opens the original)

    Episode notes

    Read excerpt

    "አፍሪካውያን የራሳቸውን ውሳኔ በራሳቸው የመወሰን ስትራቴጂካዊ ነፃነት ሊኖራቸው የሚችለው ለራሳቸው የሰላምና የልማት ጥረቶች የገንዘብ አስተዋፅኦ ማድረግ ሲችሉ ብቻ ነው። በውጭ ፋይናንስ ላይ ጥገኛ ከሆንክ የሀሳብህ ባለቤት መሆን አትችልም።" ሲሉ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የአፍሪካ ጉዳዮች ምርምር ዋና ዳይሬክተር ጋሻው አይፈራም (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ ቻይና፣ ሩሲያ፣ ቱርክ፣ የባህረ ሰላጤው ሀገራት፣ ህንድ፣ ፓኪስታን እንዲሁም የምዕራባውያን ሀገራት እጃቸውን ወደ ቀይ ባህርና ኤደን ባህረ-ሰላጤ በሰፊው እያዘረጉ ባለበት በዚህ ወቅት የአፍሪካ ቀንድ የትኩረት ማዕከል መሆኗን ዳግም አረጋግጧል ። በዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፣ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት (IFA) የአፍሪካ ጉዳዮች ምርምር ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን ዶ/ር ጋሻው አይፈራምን ጋብዘን

  2. Episode · Aug 26, 2026

    ከመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት እስከ አህጉራዊ ደህንነት፦ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እንዴት ለአፍሪካ መከታ ሆነ? (opens the original)

    Episode notes

    Read excerpt

    በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን በክፍል አንድ በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣው ግጭት፣በቀይ ባህር አቅራቢያ የሚታየው የውጭ ኃይሎች ወታደራዊ መገኘት እና የባህርላይ የንግድ መስመሮች መስተጓጎል በምስራቅ አፍሪካ ኢኮኖሚና ደህንነት ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ምንድንነው? ስንል በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናት ረዳት ፕሮፌሰር ሙከረም ሚፍታህ (ዶ/ር) አስተያየታቸውን አጋርተውናል። ከታሪካዊው የአድዋ ድል እስከ ዘመናዊው የኒዮ-ኮሎኒያሊዝምተፅዕኖ እና የ '' ኖ ሞር እንቅስቃሴ'' የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ማስከበር የመላው አፍሪካን ነፃነት እና ክብር የማስጠበቅ ያህል የሚቆጠረው ለምንድንነው? ስንል ታዋቂው የታሪክ ተመራማሪ አህመድ ዘካሪያን በጉዳዩ ላይ ሰፊ ማብራሪያ እና ታሪካዊ ትንተና ይሰጡናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም

  3. Episode · Aug 21, 2026

    የስፔስ ቴክኖሎጂ፡ የአፍሪካ ስትራቴጂካዊና መጻኢ እድል (opens the original)

    Episode notes

    Read excerpt

    "የስፔስ ቴክኖሎጂ እዚሁ ቤታችን ነው፣ አጠገባችን ነው ያለው። ግብርናችን ጋር አለ። የምንሳፈርበት ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ አለ። የስፔስ ቴክኖሎጂ ያልገባበት ቦታ የለም።... ያለ ስፔስ ቴክኖሎጂ ወደፊት መሄድ አንችልም ማለት ነው።... ስለዚህ የስፔስ ቴክኖሎጂ ሁሉ ነገራችን እየሆነ መጥቷል።" ሲሉ የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ እና ጂዮስፓሺያል ኢንስቲቱት ም/ል ዋና ዳይሬክተር ይሽሩን አለማየሁ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታቸን አፍሪካ በህዋ ሳይንስ ያላትን አዲስ ምዕራፍ እና በምስራቅ አፍሪካ እየተገነቡ ያሉ ወታደራዊ ትብብሮችን በጥልቀት እንመረምራለን። ክፍል አንድ፦ ዩሪ ጋጋሪን ወደ ህዋ ከመጠቀ ከ65 ዓመታት በኋላ፣ አፍሪካ በሳተላይት ቴክኖሎጂ ያላት ተሳትፎ የት ደረሰ? የኢትዮጵያ ETRSS 2 ሳተላይት ምጥቀትስ ለአህጉራዊ አጋርነ

  4. Episode · Aug 21, 2026

    ከነዳጅ ጥገኝነት ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል፤ ከባለአንድ ወገን ተፅዕኖ ወደ ብሪክስ ቤተሰብ (opens the original)

    Episode notes

    Read excerpt

    "ከባድ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቴክኖሎጂን ከመሞከር ወጥተን ወደ ሥርዓታዊ ኢኮኖሚ መሸጋገራችንን ያሳያሉ። በአገራችን ከ60% እስከ 70% የሚሆነውን የምርትና አገልግሎት እንቅስቃሴ የሚይዙት እነዚህ በመሆናቸው፣ ሽግግሩን ስኬታማ ለማድረግ የትራንስፖርት፣ የኢነርጂ እና የኢንዱስትሪ ፖሊሲዎቻችንን ማጣጣም አለብን።" ሲሉ ከ ፍተኛ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ኤክስፐርት በረከት ተስፋዬ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በዓለም አቀፍ ፖለቲካ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ እየከፈተች ነው። በዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ መሰናዶአችን ሁለት ሀገራዊ ፋይዳቸው የላቁ ጉዳዮችን ይዘንላችሁ ቀርበናል፦ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች አብዮት፦ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ያደረጋትን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ንቅናቄ በተለይም ወደ ከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች (Heavy EVs) የምታ

  5. Episode · Aug 21, 2026

    የስነ-ጽሁፍ ሚና በማንነት እና በታሪክ ንቃተ-ህሊና ግንባታ (opens the original)

    Episode notes

    Read excerpt

    "ወደ ዘመናዊ ስነጽሁፍ ስንመጣ ዘመናዊ ስነጽሁፍ በአብዛኛው በቴክኒኩ የውጪውን ፈለግ የተከተለ ስለሆነ ኢትዮጵያዊነት አሻራን በቴክኒኩ ላይ ማግኘት ያስቸግራል፤ ያው በጭብጡ ወጣም ወረደ ኢትዮጵያዊ ባህል ነው፣ ኢትዮጵያዊ ማንነት ነው። ... በዚህ ረገድ ቃላዊ ግጥሙ፣ ቃላዊ ትረካው በተሻለ ደረጃ ማንነታችንን በማሳየት የጎላ ባህሪ አለው።" ሲሉ በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ጽሁፍ መምህር የሻው ተሰማ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በተጨማሪም "... ፖለቲካው ላይ ያለውን ትተነው፣ መሬት ላይ ያለው ማህበረሰብ ፍቅር አለው፣ መከባበር አለው፣ መተሳሰብ አለው፤ መረዳዳት አለው፤ መደጋገፍ አለው። የሰነ-ጽሁፍ ሥራዎቻችንም ይህን አጉልተው ማሳየት አለባቸው።" ሲሉ አክለዋል። በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ መሰናዷችን በ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የስነ-ጽሁፍ መምህር ከሆኑት የሻው ተሰማ

Publishing over time

Last 90 days. Choose a month to open its work.

Recurring subjects

Named in the text we hold. One piece can cover several.

Audience

No verified audience measurement yet.

About this data

Counts cover the work we have indexed. Tone needs enough text and a confident classification. Excerpts and episode notes are not full articles or transcripts.

Identity or attribution wrong? Suggest a correction.

See coverage about The Rising South