Skip to content
HeyJared

Drum of Changes

From the heart of ancient kingdoms to the pulse of modern cities, a new rhythm echoes across the continent. Africa is rising — a formidable force shaping the world’s future. For generations, Africa has been the most spoken about, yet the least heard.

Podcast · By Zelalem Demissie · English · Official site

Indexed episodes, last 90 days
15
Latest publication
Sep 19, 2026
Audience
Checking…
Earliest in this view
Jul 8, 2026

Latest episodes

  1. Episode · Sep 19, 2026

    የአፍሪካ አረንጓዴ ጎህ፡ የማዕድን እሴትና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት (opens the original)

    Episode notes

    Read excerpt

    የዛሬው ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በሁለት አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል። የመጀመሪያው፣ አፍሪካ ከአዳዲስ ዓለም አቀፍ ጥምረቶች እና ከሻንጋይ የትብብር ድርጅት የምታገኛቸውን ትምህርቶች ከወራቤ ዩኒቨርሲቲው የምጣኔ ሀብት መምህር መሐመድ ኢሳ ጋር የምንዳስስበት ነው። ሁለተኛው ደግሞ፣ አፍሪካ ልማትና የድህነት ቅነሳን ሳታስተጓጉል ወደ ንጹሕ የኃይል አማራጭ የምታደርገውን ሽግግር ይመለከታል። በጉዳዩ ላይ ሪቻርድ ሚዩንጊ (ዶ/ር) እና ከተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ማሪት ቅጣው አስተያየታቸውን ሰጥተውበታል።

  2. Episode · Sep 17, 2026

    የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት እና በአፍሪካ ሴቶች ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ (opens the original)

    Episode notes

    Read excerpt

    በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በሩቅ የሚከሰቱ ግጭቶች ከዳካር እስከ ናይሮቢ የቤተሰብ ወጪንና የገበያ እንቅስቃሴን እንዴት እየቀየሩ እንደሆነ ከታዋቂ የመብት ተሟጋች ጋር ዳስሰናል። የዓለም አቀፍ አደጋዎችን አህጉራዊ ተፅዕኖና የሴቶችን የኢኮኖሚ ጫና በጥልቀት የምንመረምርበትን ዝግጅት እንድትከታተሉ እንጋብዛለን። ለዚህም ናይጄሪያዊቷን የመብት ተሟጋች ፋዴኬሚ አኬንፌዳሪንን አነጋግረናል።

  3. Episode · Sep 16, 2026

    ከኔቶ ባሻገር፡ ደህንነት፣ ሉዓላዊነት እና አፍሪካ እየተለወጠ ባለው ዓለም ውስጥ ያላት ቦታ (opens the original)

    Episode notes

    Read excerpt

    አሜሪካን ማዕከል አድርጎ የሚንቀሳቀሰው የኢንዶ-ፓስፊክ ስትራቴጂ ኔቶን ወደ አዲስ የውድድር አውድ እንዲገባ እያደረገው ይገኛል። ይህ ደግሞ መረጋጋትን ሳይሆን አዲስ ቅራኔን ብቻ ነው የሚጋብዘው። “አሁን እኮ የኔቶ ዓላማ የጂኦ-ፖለቲካዊ ተጽዕኖ መፍጠሪያ እና ማሰፋፊያ ወደ መሆን አዘንብሏል [...] የአፍሪካ ሉዓላዊነት የሚረጋገጠው በኢኮኖሚ ነፃነት እና በራሷ የንግድ ማዕቀፎች እንጂ ከውጭ በሚመጡ ውሱን እርዳታዎች ብቻ አይደለም […] እኛ አፍሪካውያን የምንፈልገው አካታች የዓለም ሥርዓትን እንጂ አዲስ የቀዝቃዛ ጦርነት ውጥረት አይደለም” በማለት በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲ መምህር እንዳለ ንጉሴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ኔቶ ወደ እስያ-ፓስፊክ የሚያደርገው ስትራቴጂካዊ መስፋፋት ከብሪክስ እያደገ ከመጣው

  4. Episode · Sep 16, 2026

    በብራና የተጻፈ፡ የኢትዮጵያ ሕያው የሥልጣኔ መዝገብ (opens the original)

    Episode notes

    Read excerpt

    የዛሬው የ ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ትኩረት ከነሓሴ 28፣ 2018 ዓ.ም. እስከ መስከረም 3፣ 2019 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ባለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የብራና መጻሕፍት ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን ላይ ነው። በዚሁ ጉዳይ ላይ የሐመር ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ትንሳኤ ተስፋሚካኤልን እና የፕሮጀክት ማናጀሯን ቃልኪዳን ብርሃኑን አነጋግረናል።

  5. Episode · Sep 16, 2026

    ከቃል ኪዳን ወደ ትግበራ ኃይል፡ የአፍሪካ የአየር ንብረት አጀንዳ (opens the original)

    Episode notes

    Read excerpt

    በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ከባድ ድርቅና ጎርፍ የዜጎችን የዕለት ተዕለት ኑሮ ከመፈተኑ ጀምሮ፣ እስከ ታላላቅ የድርድር መድረኮች ቃላት ከድርጊት የሚበልጡበትን አዝማሚያ ጨምሮ፣ አፍሪካ የአየር ንብረት ሉአላዊነቷን ለማስከበር የምታደርገውን የረጅም ጊዜ ትግል ታላቅ ታሪክ አካል አድርገን እናቀርበዋለን። ዝግጅቱን ከ 14ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥና ልማት ጉባኤ አንጻር የምናቀርበው ሲሆን፣ በጉባኤ ላይ ተገኝተን ዮሴፍ አመሓን (ዶ/ር)፣ በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የአየር ንብረት ተማራማሪ ጨምሮ የተለያዩ ተሳታፊዎችን አውርተናል።

Publishing over time

Last 90 days. Choose a month to open its work.

Recurring subjects

Named in the text we hold. One piece can cover several.

Audience

No verified audience measurement yet.

About this data

Counts cover the work we have indexed. Tone needs enough text and a confident classification. Excerpts and episode notes are not full articles or transcripts.

Identity or attribution wrong? Suggest a correction.

See coverage about Drum of Changes